Views: 0
ግንቦት 1/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ የብልፅግና ቤተሰብ አባላት “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” በሚል ርዕስ በተዘጋጀ የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ-ሀሳብ በሆነው ልሳነ-ብልፅግና መጽሔት ላይ ውይይት ተካሄደ።
ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት የመሻገር ጉዟችን ላይ ትኩረቱን አድርጎ የተዘጋጀው የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሀሳብ ልሳነ-ብልፅግና መጽሔት ቅፅ 1 ቁጥር 6 ላይ ጥልቀት ያለው ውይይት ተካሂዷል።
የውይይት መድረኩን የመሩት የቢሮው የሳይንስና ቴክኖሎጂ የብልፅግና ቤተሰብ ሰብሳቢ አቶ ዘላለም ጳውሎስ እንደተናገሩት ፓርቲያችን ብልፅግና ሀገራችንን ወደ ሁለተናዊ ብልፅግና የተረጋገጠባት ሀገር እንድትሆን ከተነደፉ ማዕቀፎች መካከል አንዱ የሆነው ከተረጂነት ወደ ምርታማነት መሸጋገገር መሆኑን ገልጸዋል
የፓርቲያችን አባላት አቅም ለመገንባት በየጊዜው የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሀሳብ መጽሔት ተዘጋጅቶ እየቀረበ መሆኑን አቶ ዘላለም በመጥቀስ የአሁኑ ዙር መጽሔት ልዩ የሚያደርገው ለሀገራችን ብሎም ለክልላችን ወሳኝ የሆነ አጀንዳ በመሆኑ በሚገባ ተረድቶ ተግባር ላይ መዋል እንደሚያስፈልግ ገልጸዋል።
የብልፅግና ፓርቲ ንድፈ ሀሳብ መጽሔት በቅፅ 1 በቁጥር 6 ዕትም ከተረጂነት ወደ ምርታማነት ለተሟላ ሀገራዊ ሉዓላዊነት የመሻገር ጉዟችን፤ ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በሚደረገው ሽግግር ሀገራዊ ቁመናችን እና ተረጂነት እና እርዳታ ጥገኝነት እሳቤያዊ እና አሁናዊ ሁኔታችን እንዲሁም የተሟላ የማክሮ ኢኮኖሚ ሪፎርም እርምጃዎችና እንድምታው በሚል ርዕስ የተካተቱ ሃሳቦች በንባብ ቀርቦ ሰፊ ውይይት ተደርጓል።