karat site

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል የካራት ማዕከል የክልል ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና የተስፋ ብርሃን የብልጽግና ህብረት አባላት በካራት ክላስተር የሚገነባውን የቢሮዎች ህንፃ ግንባታ ያለበትን ደረጃ የመስክ ምልከታ አደረጉ፣

Views: 2

‎‎መስክ ምልከታው የተካሄደው የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ህብረት “ከምርጫ ድል ማግስት ጠንካራ መንግስት” በሚል መሪ ቃል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ጎን ለጎን ሲሆን፣ ተሳታፊዎቹ የፕሮጀክቱን የአፈጻጸም ሁኔታ በአካል ተመልክተዋል።

‎በLEC ኢንጂነሪንግ እየተገነባ ያለው የካራት ክላስተር ማዕከል የክልል ቢሮዎች ሕንፃ ለክላስተሩ የመንግሥት አገልግሎቶችን በአንድ ማዕከል ለማቅረብ ከሚያስችሉ መሠረተ ልማቶች መካከል አንዱ መሆኑ ተገልጿል።

‎በምልከታው ወቅት የፕሮጀክቱ የአፈጻጸም ደረጃ ከሌሎች ተመሳሳይ ፕሮጀክቶች ጋር ሲነጻጸር አንስተኛ መሆኑ ተጠቁሞ፣ ግንባታው በተያዘለት ጊዜ ውስጥ ተጠናቆ ወደ አገልግሎት እንዲገባ የሥራው ፍጥነት እንዲጨምር አስፈላጊ መሆኑ ተመላክቷል።

‎‎በመስክ ምልከታው የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤና የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ ክቡር አቶ ዳርጌ ዳሼ፣ የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ክብርት ወ/ሮ ወይንቱ መልኩን፣የብልጽግና ፓርቲ ምክርቤት አባልና የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ዳኜ ሂዶ፣ እንዲሁም የተለያዩ ቢሮዎች ምክትል ኃላፊዎችና የተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት አባላት ተሳትፈዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *