‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ኢኖቬሽን ቤተሰብ “ክልላዊ የተቋማት ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ወራዊ የቤተሰብ ውይይት አካሄዱ፣

Views: 0

ካራት፣ ጥር 06/2018 ዓ.ም (ኢቴ ቢሮ)

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ የብልጽግና ፓርቲ ኢኖቬሽን ቤተሰብ “ክልላዊ የተቋማት ሪፎርም ለሁለንተናዊ ብልጽግና” በሚል መሪ ሀሳብ ወራዊ የቤተሰብ ውይይት አካሄደዋል።

‎የቢሮው ኢኖቬሽን ቤተሰብ ሰብሳቢ ህብረት አታራ (ዶ/ር) የውይይት ሰነድ ዓላማ የተሳለጡ ተቋማት መገንባት የሚያስችል የአመራሩና የአባሉ የአስተሳሰብና የተግባር አንድነት ሚና ለሁለንተናዊ ለዉጥ ወሳኝነት ለማረጋገጥ እንደሆነ ገልጸዋል።

‎የተመዘገቡ አጓጊ ጅምር የልማት ውጤቶች እንድሰፉ እና ሁሉም ህዝብ በየደረጃው በልፋቱ ልክ ተጠቃሚ እንድሆን የፓርቲያችን አመራርና የአባላት የበኩሉን ድርሻ ልወጣ ይገባል ብለዋል።

‎ጠንካራ የአሰራር ስርዓት በመዘርጋት ሀብትን ለታለመለት ዓላማ ብቻ የሚያዉሉ ብክነትን ወሳኝ በሆነ መልኩ በመቀነስ ሌብነትና ብልሹ አሰራርን በትግል ያከሰሙ ተቋማት መገንባት እንደሚገባም ዶ/ር ህብረት አስገንዝበዋል።

‎የፓርቲው መደበኛ፣ ልዩ እና የህንፃ ግንባታ መዋጮዎች ለፓርቲው ዓላማ ስኬት መሠረታዊ በመሆናቸው ሁሉም አባላት የበኩሉን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል።

‎በውይይቱ መድረክ ከአባላቱ በተነሱ ጥያቄና አስተያየት ዙሪያ የቤተሰቡ ስብሳቢ ህብረት አታራ (ዳ/ር) ምልሽና ማብራሪያ በመሰጠት የዕለቱ ውይይት ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *