dr hibert

በቴክኖሎጂ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን በፈጠራ ሥራዎች ማስተሳሰር እንደሚገባ ተገለፀ።

Views: 0

በቴክኖሎጂ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን በፈጠራ ሥራዎች ማስተሳሰር እንደሚገባ ተገለፀ።

ታህሳስ 14/2018 ዓ.ም (ኢቴ ቢሮ) ፦

በሣውላ ከተማ ኩስቲ ቁጥር አንድ አንደኛና መለስተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሳይንስ ቀንን ምክንያት በማድረግ የተለያዩ የፈጠራ ስራዎችን ለዕይታ አቅርቧል ።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ምክትልና የኢኖቬሽንና ምርምር ዘርፍ ኃላፊ ዶክተር ህብረት አታራ እንደተናገሩት ተማሪዎች የሚያቀርቧቸው የፈጠራ ሥራዎች የተጀመረውን ዲጂታል ኢትዮጵያ እውን ለማድረግ አጋዥ መሆኑን ገልጸዋል

በሀገሪቱ የትምህርት ሥርዓት ውስጥ ተማሪዎች የሳይንስ እውቀታቸውን እንዲያዳብሩ ለማስቻል በርካታ ተግባራት እየተከናወኑ እንደሚገኙ አስረድተዋል ።

በትምህርት ቤቶች የፈጠራ ባለቤት የሆኑ ተማርዎችን ማበረታታትና አስፈላጊውን ሁሉ በማመቻቸት የዘርፉ አካላት በቅንጂት ሊሰሩ ይገባልም ብለዋል፡፡

የጎፋ ዞን ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ መምሪያ ኃላፊ አቶ ጳውሎስ ፋይሌ በበኩላቸው በቴክኖሎጂ የበለጸገች ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የመማር ማስተማር ሂደቱን በፈጠራ ሥራዎች ማስተሳሰር የነገዋን ኢትዮጵያ ለመገንባት ዓይነተኛ ሚና ያለው መሆኑን ገልጸዋል ።

ተማሪዎች የፈጠራ ሥራቸውን በተለያዩ አጋጣሚዎች እንዲያቀርቡ ማድረግ በተማሪዎቹ መካከል የልምድ ልውውጥ ለማድረግና ሥራዎቻቸውን ለማስተዋወቅ የሚጠቅም በመሆኑ ተማሪዎቹን ተከታትሎ በመደገፍ ረገድ በትኩረት መስራትን ይጠይቃል ብለዋል ፡፡

የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ሥራዎች በርካታ ጠቀሜታ የሚያስገኙ ሲሆኑ ተማሪዎች ስራ ፈጣሪ እንዲሆኑ ትልቅ መነቃቃትን የሚፈጥር መሆኑን አክለው ገልጸዋል ።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂው ዘርፍ ማተኮር ሀገራዊ ፋይዳው ከፍተኛ በመሆኑ በተማሪዎች ፈጠራ ሥራ ላይ በትኩረት መስራት አስፈላጊ እንደሆነ ነው በመድረኩ የተመላከተው ፡፡

በዚህም መሠረት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽን እና ቴክኖሎጂ ቢሮ በትምህርት ቤቱ የፈጠራ ችሎታ ያላቸውን ተማሪዎችን የፈጠራ ስራ የሚያበረታታ የሳይንስ ኪት ድጋፍ አድርጓል።

ዘገባው: የሣውላ ከተማ መንግሥት ኮሙዩኒኬሽን ነው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *