Views: 1
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በ2019 ዓ.ም የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ዕቅድና በቀሪ ወራት ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።
በዚሁ መድረክ የተቋሙ የወደፊት የስራ አቅጣጫ እና የአፈፃፀም ብቃት የሚያሻሽሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማኔጅመንቱ በሰፊው ተወያይተዋል።
በተጨማሪም ማኔጅመንቱ በፀደቀው የክልል ማዕከል የሴክተር መስሪያ ቤቶች የመንግሥት ሰራተኞች የድልድል ዙሪያ ውይይት አድርጎ የአፈፃፀም አሻሻይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፣ በሁሉም የልማት ዘርፎች ውጤታማነትን ለማሳደግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፉ ተቋማትን መፍጠር ወሳኝ ሲሆን፣ ለተቋሙ የሚመደበው የ2019 ዓ.ም የመደበኛና ካፒታል በጀት በዚህ አቅጣጫ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።
እንዲሁም ተግባራት በተፈለገው ደረጃ እንዲፈጸሙ የተሟላ የሰው ሀይል አቅርቦት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቦጋለ በዚህም መሠረት የሴክተር መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ድልድል አፈፃፀምን ለማስጀመር ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር እንዲገባ መመሪያ ተሰጥቷል። በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም ቀሪውን ሶስት ወራት በከፍተኛ ውጤት ለማጠናቀቅ ከዚህ በኋላ ቅዳሜ ቀንም እንደ መደበኛ የስራ ቀን ሆኖ እንዲውል መወሰኑን ኃላፊው ገልፀዋል