Views: 0
ካራት፣ ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም
በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የካራት ማዕከል ተስፋብርሃን የብልጽግና ኅብረት የ3ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ እየተካሄደ ይገኛል።
በመድረኩም የኅበረቱ ሰብሳቢ አቶ ዳርጌ ባሼ በካራት ማዕከሉ ለሚገኘው አመራሮችና አባላት ለውይይት የ3ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሰነድ እየቀረበ ይገኛል።
በመድረኩ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳዬ፣ የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ፣ ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ እና የካራት ማዕከል የብልጽግና ኅብረት አባላት ተሳታፊ ሆነዋል።