Views: 1

ካራት፣ ግንባት 19/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አጠቃላይ አመራሮች፣ ማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች ኢትዮ ኮዳርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ጨርሳ ተመርቀዋል።
የኦንላይን ሥልጠና በዌብ -ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እንዲሁም እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ተቀብለዋል።
አጠቃላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠናውን በትኩረት እንድከታተል በቡድን በመከፋፈልና የሚከታተል የቡድን ተጠሪ በመመደብ በመሆኑ ተገልጿል።
የቡድን ተጠሪዎች ሰልጣኞች የደረሱበትን በየቀኑ ሪፓርት በማድረግና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቢሮው ለቡድን መሪዎች እውቅናና ማበረታቻ ተሰጥቷል።
ሠልጣኞች ነጻ የኦንላይን ስልጠና በመከታተል ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ አስታያየት በሰጡት ወቅት ገለጸዋል።
በመጨረሻም ቢሮው ምክትል ኃላፊና ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ፍቃዱ በየነ የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ስልጠና ዕድሎች ተጠቃሚ እዲሆኑ https://ethiocoders.et/ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ተሰጥዎን በማውጣት፤ ነገን እንለውጥ!