Views: 1
ካራት ነሐሴ፣ 13/2017 ዓ/ም (ኢቴ ቢሮ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (ቢፒአር) ክለሳ ጥናት ተጠናክሮ መቀጠሉን ተገልጸዋል።
የቢሮው ጥናት ቡድን የደረሰበትን ደረጃ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና የካራት የክላስተር አሰተባባሪ አቶ አዳማ ትንጳዬ እና የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሱፐርቪዥን አደርገዋል።
የቢሮው የመሰረታዊ የሥራ ሂደት ለውጥ (ቢፒአር) ክለሳ ጥናት ቡድን እስካሁን የደረሰበት መረጃ በቡድን አስተባባሪ ገለጻ ለሱፐርቪዥን አካላት ከተደረገ በኋላ በቀጣይ ተግባራት ዙሪያ ሰፋ ያለ ውይይት አደርገዋል።
የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤና የካራት የክላስተር አሰተባባሪ አቶ አዳማ ትንጳዬ የሰጡት አስታያየት ቡድኑ የክልሉ ፐብሊክ ሰርቪስና የሰው ሀብት ኮሚሽን ባስቀመጠው ጊዜ ገደብ ለመጨረስ እስካሁን የተሻለ ደረጃ መድረሱና የተሻለ ስራ መስራቱን ገልፀዋል።
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ትልቅ ሀላፊነትና ታሪካዊ ጥናት ስለሆነ በጣም ጥንቃቄ በተሞላበት ጥናት እንዲያደርጉና ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ጥናቱን እንዲጨርሱ አሳስበዋል።
#ዘገባው የቢሮው ኮሙኒኬሽንና ሚዲያ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ነው።