ato tekalign

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አጠቃላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ኢትዮ ኮዳርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ጨርሳ ተመረቁ፣

Views: 1

ካራት፣ ግንባት 19/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ አጠቃላይ አመራሮች፣ ማኔጅመንት አካላትና ባለሙያዎች ኢትዮ ኮዳርስ ኢኒሼቲቭ ስልጠና ጨርሳ ተመርቀዋል።

‎የኦንላይን ሥልጠና በዌብ -ፕሮግራሚንግ፣ በአንድሮይድ ማበልፀግ፣ ዳታ ሳይንስ እንዲሁም እና በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት ተቀብለዋል።

‎አጠቃላይ አመራሮችና ባለሙያዎች ስልጠናውን በትኩረት እንድከታተል በቡድን በመከፋፈልና የሚከታተል የቡድን ተጠሪ በመመደብ በመሆኑ ተገልጿል።

‎የቡድን ተጠሪዎች ሰልጣኞች የደረሱበትን በየቀኑ ሪፓርት በማድረግና የቴክኒክ ድጋፍ በማድረግ ላደረጉት አስተዋጽኦ ቢሮው ለቡድን መሪዎች እውቅናና ማበረታቻ ተሰጥቷል።

‎ሠልጣኞች ነጻ የኦንላይን ስልጠና በመከታተል ዓለም አቀፍ ተቀባይነት ያለው ሰርተፊኬት በመቀበላቸው የተሰማቸውን ደስታ አስታያየት በሰጡት ወቅት ገለጸዋል።

‎በመጨረሻም ቢሮው ምክትል ኃላፊና ፋይናንስና አስተዳደር ዘርፍ ኃላፊ ፍቃዱ በየነ የኮዲንግ መሠረታዊ ክህሎት ለማዳበር የሚያስችሉ ነጻ የኦንላይን ስልጠና ዕድሎች ተጠቃሚ እዲሆኑ https://ethiocoders.et/ እንዲመዘገቡ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

‎ተሰጥዎን በማውጣት፤ ነገን እንለውጥ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *