ato tekalign

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ለመላው የኮንሶ ማህበረሰብ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፉ፣

Views: 1

ካራት ሰኔ 20/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)

‎ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ለመላው የኮንሶ ማህበረሰብ እንኳን “ለኾራ ኣታ ኾንሶ” ክብረ – በዓል በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል።

‎የኮንሶ ህዝብ ታታሪነት አለም የመሰከረለት፣ የተፈጥሮ ገጸ በረከት፣ ባህላዊ ዕሴቶች፣ የሰዉ ሰራሽና የተፈጥሮ ቅርሶች ባለቤት ነው።

‎የህብረተሰቡ የስራ ታታሪነት፣ በተራራ፣ በእርከን ስራና በአምባ መንደራት ላይ የታዩ በእጅ የተሰሩ የማይመስሉ የምህንድስና ጥበብ እጅግ የሚደነቅና በአለም አቀፍ ደረጃም እንዲታወቅ ያደረገበት በዓል በመሆኑን በመልዕክታቸው ።

‎አቶ ተካልኝ በመልዕክታቸው በኮንሶ ማህበረሰብ ዘንድ “የአንድነታችንና የታታሪነታችን መገለጫ “በሚል መሪ ቃል ዘንድሮ በመላው የኮንሶ ማህበረሰብ ዘንድ በልዩ ዝግጅትና ድምቀት ለሚከበረው ክብረ – በዓል እንኳን በሠላም አደረሳችሁ/አደረሰን ብለዋል።

‎በዓሉ የሠላም፣ የፍቅር፣ የአብሮነት፣ የመተሳሰብ እና የማህበረሰቡ ባህላዊ እሴቶች ይበልጥ ጎልተው የሚወጡበት እንዲሆንም ከልብ ተመኝተዋል።

‎ መልካም በዓል!!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *