meeting

በ2017 በጀት ዓመት ቢሮው ባከናወነው ተግባራት ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ሊወጣ የነበረ የመንግስት ሃብት ማዳን መቻሉ ተገለፀ፣

Views: 0

ካራት፣ ሰኔ 25/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት አካላት የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ።

‎በቢሮው የልማት ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካምባታ ካዌ የቢሮውን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለማኔጅመንቱ አቅርበዋል።

‎በበጀት ዓመቱ ቢሮው ባከናወነው ተግባራት በኢኮቴ መሣሪያዎች ጥገናና አማራጭ ቴክኖሎጂን /ዙም ሚቲንግ/ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ሊወጣ የነበረ የመንግስት ሃብት ማዳን መቻሉን ተገለጿል።

‎የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭን ለማሳካት ከ62 ሺህ በላይ ‎ኮደርሶችን የተመዘገቡ መሆኑንና ከ23 ሺህ በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው ሰርተፍኬት ወስደዋል።

‎በክልሉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርአቱን እንዲሳለጥ እና የተቋማትን አገልግሎት የሚያቀላጥፉ 7 ሲስተሞችንና 23 ዌብሳይቶችን የማልማትና የማላመድ ስራ ተሰርቷል።

‎የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት በጨረራ አመንጪ መሳሪዎች የሚመነጭ ጨረር የጎንዮሽ ጉዳት ለመከላከልና ደህንነቱን ለማረጋገጥ 2 ዙር ኢንስፔክሽን ማድረግ የተቻለ ሲሆን ለ3 ተቋማት የጨረር አመንጪ መሳሪያዎች የመጠቀም ፍቃድ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።

‎የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱና የፈጠራ ዝንባሌያቸውን ተማሪዎች እንዲያሳድጉ የትምህርት ቤቶች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን የቴክኒክና የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።

‎ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ባለስልጣን ጋር በመሆን ስድስት ግለሰቦችና ተቋማት የአዕምሯዊ ንብረት ዕውቅና እና ዕድሳት እንዲያገኙ መደረጉን በሪፖርቱ ተገምግሟል።

‎በግምገማ ወቅት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለፀው ከማኔጅመንት አካላት ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *