Views: 0
ካራት፣ ሰኔ 25/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት አካላት የተቋሙን የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድ አፈጻጸም ግምገማ አካሄዱ።
በቢሮው የልማት ዕቅድና በጀት ዝግጅት፣ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ካምባታ ካዌ የቢሮውን የ2017 በጀት ዓመት አፈጻጸም ሪፖርት ለማኔጅመንቱ አቅርበዋል።
በበጀት ዓመቱ ቢሮው ባከናወነው ተግባራት በኢኮቴ መሣሪያዎች ጥገናና አማራጭ ቴክኖሎጂን /ዙም ሚቲንግ/ ከ23 ሚሊዮን ብር በላይ ሊወጣ የነበረ የመንግስት ሃብት ማዳን መቻሉን ተገለጿል።
የኢትዮ ኮደርስ ኢንሼቲቭን ለማሳካት ከ62 ሺህ በላይ ኮደርሶችን የተመዘገቡ መሆኑንና ከ23 ሺህ በላይ የሚሆኑት ስልጠናውን አጠናቀው ሰርተፍኬት ወስደዋል።
በክልሉ የዲጂታል ኢኮኖሚ ስርአቱን እንዲሳለጥ እና የተቋማትን አገልግሎት የሚያቀላጥፉ 7 ሲስተሞችንና 23 ዌብሳይቶችን የማልማትና የማላመድ ስራ ተሰርቷል።
የመንግስትና የግል ጤና ተቋማት በጨረራ አመንጪ መሳሪዎች የሚመነጭ ጨረር የጎንዮሽ ጉዳት ለመከላከልና ደህንነቱን ለማረጋገጥ 2 ዙር ኢንስፔክሽን ማድረግ የተቻለ ሲሆን ለ3 ተቋማት የጨረር አመንጪ መሳሪያዎች የመጠቀም ፍቃድ የተሰጠ መሆኑ ተገልጿል።
የማህበረሰቡን ችግር እንዲፈቱና የፈጠራ ዝንባሌያቸውን ተማሪዎች እንዲያሳድጉ የትምህርት ቤቶች ሳይንስና ቴክኖሎጂ ክበባትን የቴክኒክና የቁሳቁስ ድጋፍ የተደረገ መሆኑ በሪፖርቱ ተገልጿል።
ከኢትዮጵያ አዕምሯዊ ባለስልጣን ጋር በመሆን ስድስት ግለሰቦችና ተቋማት የአዕምሯዊ ንብረት ዕውቅና እና ዕድሳት እንዲያገኙ መደረጉን በሪፖርቱ ተገምግሟል።
በግምገማ ወቅት የቢሮው ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ በበጀት ዓመቱ በሁሉም ዘርፍ የተሻለ አፈጻጸም ማስመዝገቡን ገለፀው ከማኔጅመንት አካላት ለተነሱ ሀሳቦች ማብራሪያ በመስጠት የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።