የካራት ማዕከል ተስፋብርሃን የብልጽግና ኅብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት ጠቅላላ አባላት ኮንፈረንስ መድረክ ተጠናቀቀ፣

Views: 0

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም (ሳኢቴ ቢሮ)

‎በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት የካራት ማዕከል ተስፋብርሃን የብልጽግና ኅብረት የ2017 በጀት ዓመት 3ኛ ሩብ ዓመት ጠቅላላ አባላት ስካሄድ የነበረው ኮንፈረንስ መድረክ ተጠናቋል።

‎የክልሉ ብሔረሰቦች ምክር ቤት ዋና አፈ ጉባኤ አቶ አዳማ ትንጳዬ በመክፈቻ ንግግር ባደረጉት ወቅት ፓርቲው በኢኮኖሚ፣ በማህበራዊና በፖለቲካ መስኮች በርካታ ስኬቶችን ማስመዘገብ የቻለና ሀገርን ከፈተናና ከመፍረስ ታድጎ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ እየሰራ የሚገኝ ፓርቲ ነው ብሏል።

‎በመድረኩም የኅበረቱ ሰብሳቢ አቶ ዳርጌ ዳሼ በካራት ማዕከሉ ለሚገኘው አመራሮችና አባላት ለውይይት የ3ኛ ሩብ ዓመት አፈፃፀም ሰነድ ከቀረበ በኋላ ውይይት ተደርግዋል።

‎በመድረኩ የኅብረቱ የ2017 ዓ/ም 3ኛ ሩብ ዓመት ዕቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ባቀረቡበት ወቅት የኅብረቱ ሰብሳቢ አቶ ዳርጌ ዳሼ በዘርፉ የተሰሩ ጠንካራ ሥራዎችን በማስቀጠል በጉድለት የተለዩትን በማረም የብልጽግና ጉዟችን ማሳካት ይገባል ብለዋል።

‎የሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ ሁለንተናዊ ብልጽግና ለማረጋገጥ የሚደረገው ጉዞ ጠንካራ ፓርቲ አባል መገንባት ወሳኝ መሆኑን ተናግረዋል።

‎አክሎም የብልጽግና ፓርቲን ከማጠናከርና ከመትከል አኳያ መነሻ የሆነውን ብልጽግና ፓርቲ ኅብረት ቤተሰብ አመራሮች ለፓርቲ አባላት ሞዴል በመሆን የመንግስትና የፓርቲ ግንባታ ሥራዎችንና ተልዕኮዎችን በተገቢው ማጠናከርና መስራት እንደሚገባ ገልጸዋል።

‎ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ወይኒቱ መልኩ በበኩላቸው ባለፉት ወራት የፓርቲ ስራን ውጤታማ ለማድርግ በርካታ ተግባራት መከናወናቸውን የገለፀው የተስተዋሉ ጉድለቶችን ፈጥኖ በማረም ጥንካሬዎችን በማጎልበት እና ቀጣይ የህዝብ ተጠቃሚነትን ለማረጋገጥ የተሻለ የፓርቲና የመንግስት ተቋማት ግንባታ ላይ በትኩረት ልሰራ ይገባል ብሏል።

‎በውይይቱ ተሳታፊዎች የተለያዩ ሀሳብ አስተያየትና ጥያቄዎች ተነስቶ ከመድረክ በሚመለከታቸው አካላት ምላሽና ማብራሪያ ተሰጥቶ የዕለቱ መድረክ ተጠናቋል።

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ሳይንስና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ

ሚያዚያ 29/2017 ዓ.ም ካራት

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *