ato adama

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካራት ማዕከል ተስፋ ብርሀን የብልጽግና ህብረት የ2ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ አካሄደ፣

Views: 0

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ካራት ማዕከል ተስፋ ብርሀን የብልጽግና ህብረት የ2ኛ ሩብ ዓመት የአባላት ኮንፈረንስ መድረክ አካሄደ፣

ታህሳስ 15/2018 ዓ.ም (ኢቴ ቢሮ)

በመድረኩ የመክፈቻ ንግግር ያደረጉት የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ ብልጽግና ፓርቲ በዕቅዱ መሠረት ልዪ ትኩረት ለምሹ ተግባራትን በ90 ቀን ዕቅዶች እየተመራ መሆኑን አስገንዝበው፣ በቀጣይ በጊዜ የለንም መንፈስ የፓርቲና የመንግስት ተግባራትን አቀናጅቶ እንድመራ አሳስበዋል ።

የ2ኛ ሩብ ዓመት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት ያቀረቡት የብሔረሰቦች ምክር ቤት ምክትል አፈ ጉባኤ እና የህብረቱ ስብሳቢ የተከበሩ አቶ ዳርጌ ዳሼ በ2ኛ ሩብ ዓመት

ከተሰሩ ስራዎች ዉስጥ ከአባል እስከ ህብረት ዕቅዶች መታቀዱን የአረጋውያን ቤቶች ግንባታና ምገባ ተጠናክሮ እየተሰራ መሆኑንና መቀጠል እንዳለበት አንስተዋል ።

ከአባላቱ በዉይይት የተነሱ በፓርቲ አሰራር መመሪያዎችና ደንቦች ላይ ስልጠና መጠናከር እንዳለበት እንድሁም እንዴ ክላስተር በሚድያ የመንግስትና የፓርቲ ሀሳብ መሸጥ አንፃር አባሉ ተጠናክሮ መስራት እንዳለባቸው ተናግረዋል።

በቀጣይ ህብረቱ ጠንካራ እንደሆን ቤተሰብን በማጠናከርና በመደገፍ በፓርትና በመንግሥት የሚወርድ ተግባር የተሻለ አፈፃፀም ማስመዝገብ እንዳለበት ተመልክቷል።

የካራት ክላስተር ማዕከል ተስፋ ብርሃን ህብረት የፓለቲካ ዘርፍ ኃላፊ አቶ ዳኜ ህዶ በህብረቱ የተከናወኑ የሚበረታቱ ሲሆን በቀጣይ በጉድለት የተነሱ ተግባራት መታረም እንዳለባቸው አመላክተዋል።

በመድረኩ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬን ጨምሮ ምክትል ቢሮ ሀላፊዎች የህብረቱ አመራሮችና አባላቶች ተሳትፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *