Views: 0
ቢሮው በሳይንስና ቴክኖሎጂ እና ስታርት አፕ ፓሊሲ ዙሪያ ለማኔጅመንት አካላትና ከፍተኛ ባለሙያዎች በአርባምንጭ ስልጠና ሰጥቷል።
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ቦጋለ ቦሼ (ዶ/ር)፤ መንግስት በ2030 ዲጂታል ኢትዮጵያን ለመገንባት የያዘዉ ዉጥን እንዲሳካ በየደረጃው ያሉ የዘርፉ አመራሮች በከፍተኛ ኃላፊነት መስራት እንዲችሉ ስልጠናው ያግበዛል ብለዋል።
ቢሮው ሀገራዊ ኢንሼቲቦች በክልሉ ውጤታማ እንዲሆኑ ተልዕኮ እንደተሰጠውና ይህንንም ለማሳካት በሳይንስና ቴክኖሎጂው ዘርፍ በርካታ ተግባራትን እያከናወነ እንደሚገኝ ዶ/ር ቦጋለ ጠቁመዋል።
ተቋማት አገልግሎታቸውን በቴክኖሎጂ በመደገፍና ዲጂታይዝ በማድረግ ቀልጣፋ፣ ፈጣንና እንግልትን በሚያስቀር መልኩ መፈፀም እንዲችሉ የማዘመን ስራ እየተሰራ እንደሚገኝ አብራርተዋል።
በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የዘርፍ ካውንስሎች እና ክልሎች ጉዳይ ኃላፊ አቶ ኑርልኝ ኮኩ፤ ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ብቁ የሆኑ አመራሮችን ለመፍጠር በማሰብ ስልጠናው እየተሰጠ ይገኛል ብለዋል።
አክለውም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ በአገሪቱ በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ዘርፍ የምርምርና የስርፀት ስራዎችን በመስራት በዘርፉ ተጨባጭ ለውጦች እንዲመዘገቡ እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
በስልጠናው ዙሪያ የተለያዩ ሀሳቦችና የማብራሪያ ጥያቄዎች የተሰነዘሩ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላትና ከመድረኩ ሰፊ ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቶባቸዋል።
ስልጠናው በሳይንስና ቴክኖሎጂ፣ ስታርት አፕ ፓሊሲ ዙሪያ ትኩረት ማድረጉን እና በቀጣይም በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዙሪያ ለሚያከናውኑት ተግባር አጋዥ መሆኑን ሰልጣኞቹ ጠቁመዋል።
source:- South Television and radio Agency