Views: 0
የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊና የዕለቱ ክቡር እንግዳ አቶ ተካልኝ ጋሎ ኢትዮጵያ ቀደምት የስልጣን ባለቤት መሆኗንና ይህንን አጠናክሮ ለማስቀጠል የአሁኑ ትዉልድ ከቀደም አባቶች የተረከቡትን አደራ ማስቀጠል አለባቸው ብለዋል።
ሀገርቱ በቀጠዩ በኢኮኖሚው ፖለቲካዊ እና ማህበራዊ ዘርፍ ለማሳካት ያስቀመጠችውን ራዕይ እንዲሳኩና ሀገራዊ ጥቅም ለማስከበር አመራሩ ከመቼውም ጊዜ በላይ ዝግጁ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል።
ኢትዮጵያን ለማዳከም የዉስጥ ችግር ለመፍጠርና የህዝቡን አንድነት ለመሸርሸር ከዉጭ ሀይሎች ጋር የሚሰሩ ባንዳዎችን ለመታገል አመራሩ የተግባርና አስተሳሰብ አንድነት በማቀናጀት የሚሰጡ ተልዕኮዎችን በብቃት መፈጸም አለበት ብለዋል።
የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ ብልጽግና ፓርቲ ሀገርቱን መምራት ከጀመረ ወዲህ በሀገርቱ በርካታ ተጨባጭ ለዉጦች እየተመዘገበ ይገኛል ብለዋል።
አመራሩ በስልጠናው አለምአቀፋዊ፣ ሀገራዊ፣ ቀጠናውና ክልላዊ ወቅታዊ ነባራዊ ሁኔታዎችን በደንብ ተረድቶ በተሰማራበት ሥራ ዉጤት ለማስመዝገብ ርብርብ ማድረግ እንዳለበት ገልጸዋል።
በስልጠናው መድረክ ላይ የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ አቶ ተካልኝ ጋሎ፣ የኮሬ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ በቀለ፣ የኮሬ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ቅ/ጽ/ቤት ኃላፊ አቶ ሳሙኤል ሳድሁን፣ የዞን አስተባባሪና አጠቃላይ አመራሮች፣የወረዳ እና ከተማ አስተዳደር አስተባባሪዎች በመሳተፍ ላይ ናቸዉ።