Views: 0
በሀገራችን ኢትዮጵያ ከ12 ሚሊየን በላይ እንዲሁም በዓለማችን 3.7 ቢሊየን ገደማ ንቁ ወርሃዊ ተጠቃሚዎች (Active users) ያሉት ፊስቡክ የማሕበራዊ ትስስር ገጽ፤ በርካታ መንግስታዊ እና የግል ተቋማት ምርትና አገልግሎታቸውን ተደራሽ ለማድረግ እንዲሁም ከተገልጋዮች ጋር ቅርብ የሆነ ግንኙነት ለመፍጠር ይህንኑ ፕላትፎርም ይጠቀማሉ፡፡
ይህን ያህል በርካታ ቁጥር ተቃሚዎች ያሉት የፌስቡክ ገጽ በየእለቱ ከሦስት መቶ ሺ እስከ ስድስት መቶ ሺ ያህል የፕላትፎርሙ ተጠቃሚዎችን አካውንቶችን ሰብሮ የመግባት (log in) የጥቃት ሙከራዎች ያስተናገዳሉ፡፡ በርግጥ እነዚህ የጥቃት ሙከራዎቹ ከሙከራ ሳይዘሉ በፕላትፎረሙ ጠንካራ የደህንነት ስርአት ይከሽፋሉ፡፡
እነዚህን የጥቃት ሙከራዎች ለመከላከል ተቋማትም ይሁን ግለሰቦች የሚከተሉትን የጥንቃቄ መንገዶች ተግባራዊ ማድረግ ይገባቸል፡፡