dr bogale

የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ከዚህ በኋላ ቅዳሜ ቀንም እንደ መደበኛ የስራ ቀን እንዲሆን ወሰነ፣

Views: 1

‎የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ማኔጅመንት አባላት በ2019 ዓ.ም የመደበኛና ካፒታል ፕሮጀክቶች ዕቅድና በቀሪ ወራት ተግባራት ዙሪያ ውይይት አካሂደዋል።

‎በዚሁ መድረክ የተቋሙ የወደፊት የስራ አቅጣጫ እና የአፈፃፀም ብቃት የሚያሻሽሉ ጉዳዮች ዙሪያ ማኔጅመንቱ በሰፊው ተወያይተዋል።

‎በተጨማሪም ማኔጅመንቱ በፀደቀው የክልል ማዕከል የሴክተር መስሪያ ቤቶች የመንግሥት ሰራተኞች የድልድል ዙሪያ ውይይት አድርጎ የአፈፃፀም አሻሻይ አቅጣጫዎችን አስቀምጧል። የቢሮ ኃላፊ ዶ/ር ቦጋለ ቦሼ በዚህ ወቅት እንደገለፁት፣ በሁሉም የልማት ዘርፎች ውጤታማነትን ለማሳደግ በዲጂታል ቴክኖሎጂ የተደገፉ ተቋማትን መፍጠር ወሳኝ ሲሆን፣ ለተቋሙ የሚመደበው የ2019 ዓ.ም የመደበኛና ካፒታል በጀት በዚህ አቅጣጫ ከፍተኛ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

‎እንዲሁም ተግባራት በተፈለገው ደረጃ እንዲፈጸሙ የተሟላ የሰው ሀይል አቅርቦት እጅግ አስፈላጊ መሆኑን የገለጹት ዶ/ር ቦጋለ በዚህም መሠረት የሴክተር መስሪያ ቤቱ የሰራተኞች ድልድል አፈፃፀምን ለማስጀመር ኮሚቴ ተቋቁሞ ወደ ተግባር እንዲገባ መመሪያ ተሰጥቷል። ‎በመጨረሻም የ2018 ዓ.ም ቀሪውን ሶስት ወራት በከፍተኛ ውጤት ለማጠናቀቅ ከዚህ በኋላ ቅዳሜ ቀንም እንደ መደበኛ የስራ ቀን ሆኖ እንዲውል መወሰኑን ኃላፊው ገልፀዋል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *