mircha

የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መረሃ-ግብር አካሄደ ።

Views: 0

ህብረቱ ኢትዮጵያ፣ ወደ ተምሳሌት ሀገር!!” በሚል መሪ ቃል የብልጽግና ፓርቲ የ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ መወዳደሪያ ማኒፌስቶና የምርጫ ምልክት ማስተዋወቂያ መርሃ-ግብር አካሂዷል።

‎በመረሃ- ግብሩ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤና የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዳርጌ ዳሼ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክታቸው የስንዴ ነዶ”ን የምርጫ ምልክታችን አድርገን የመረጥነው የላብ፣ የጥረትና የአንድነታችን ወካይ የድል አርማ በመሆኑ ነው ብለዋል።

‎የብልጽግና ፓርቲ ምክርቤት አባልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ፣ የብልፅግና ፓርቲ ለ7ኛው ሀገራዊ ምርጫ የሚጠቀምበት “የስንዴ ነዶ” የምርጫ ምልክት መሆኑን በመግለጽ ፓርቲው አገሪቱን ከነበረችበት የችግር ደረጃ አውጥቶ፣ ወደ ተትረፈረፈ ሀብት፣ ከፍተኛ ምርታማነትና ወደ ተሟላ ሁለንተናዊ ብልፅግና እያሸጋገረ እንደሆነ ተናግረዋል።

‎የስንዴ ነዶው የመደመር፣ የምርታማነትና በምግባ እራስን መቻል፣ የሉዓላዊነት እና የበረከት መገለጫ ሲሆን፣ በመጪው ምርጫ ሂደት አባሉ በንቃት እንዲሳተፉ እና ባለበት ማዕከል የፓርቲውን ዓላማ እንዲያስተዋውቅ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ አስገንዝበዋል።

‎በመርሃ-ግብሩ በተለያዩ ዝግጅቶች በድምቀት የተካሄደ ሲሆን፣ የብልጽግና ፓርቲ ምክርቤት አባልና የደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ብሔረሰቦች ምክርቤት ዋና አፈጉባኤ የተከበሩ አቶ አዳማ ትንጳዬ፣ የክልሉ ብሔረሰቦች ምክርቤት ምክትል አፈጉባኤና የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ዳርጌ ዳሼ፣ አቶ ዳኜ ሂዶ የብልጽግና ምክርቤት አባልና የክልሉ ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ፣ ዶ/ር ቦጋሌ ቦሼ የኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ፣ ምክትል ቢሮ ኃላፊዎች እንዲሁም የካራት ክላስተር ተስፋ ብርሃን ብልጽግና ህብረት አመራሮችና አባላት ተሳትፈዋል ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *