mesob

“በክልሉ ስራ በጀመሩ 3ቱ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት ተቋማት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ተከናውኗል” የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ

Views: 2

መሰብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ማዕከላት ድጅታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የጎላ አስተዋፅኦ እንዳለውም ተጠቁሟል

የደበብ ኢትዮጵያ ክልል ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ ኃላፊ ቦጋለ ቦሻ (ዶ/ር) በክልሉ ተገንብተው ስራ በጀመሩ የወላይታ ሶዶ ፣ የአርባምንጭ እና የዲላ መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ከ800 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ የቴክኖሎጂ ዝርጋታ ተከናውኗል ብለዋል።

ማዕከላቱ የተበታተኑ የመንግሥት ተቋማትን አሠራር በዲጂታል ትስስር በማቀናጀት፣ ከወረቀት ንክኪ የፀዳ ፈጣን አገልግሎት በአንድ ጣሪያ ሥር በመስጠት ዲጂታል ኢትዮጵያን እውን ለማድረግ የጎላ አበርክቶ እንዳለውም የቢሮው ኃላፊ አብራርተዋል።

በማዕከላቱ አገልግሎት ላይ የዋሉ ቴክኖሎጂዎች ተገልጋዮች ከቤታቸው ወይም ከሥራ ቦታቸው ሳይነጠሉ በኮምፒውተርና በስማርት ስልክ አገልግሎት እንዲያገኙ የሚያስችሉ መሆናቸውንም ዶክተር ቦጋለ ገልፀዋል።

በተጨማሪም የተገልጋዮችን የግል መረጃ ሚስጥራዊ በሆነ መልኩ ለረዥም ዘመናት እንዲቆይ የሚያስችል ከመሆኑ ባሻገር አላስፈላጊ የሰው ለሰው ንኪኪ አስቀርቶ ተአማኒነትን የሚጨምር መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አመላክተዋል።

የክልሉ ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ቢሮ በሶስቱ መሶብ የአንድ ማዕከል አገሌግሎት መስጫ ተቋማት የተከናወኑ የቴክኖሎጂ ዝርጋታዎችን የማማከር ስራ ማከናወኑንም አሳውቀዋል።

በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ወላይታ ሶዶ፣ አርባምንጭ እና ዲላ ከተማዎች መሶብ የአንድ ማዕከል አገልግሎት መስጫ ተቋማት ተገንብተው ስራ መጀመራቸው ይታወቃል

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *